Tuesday, October 18, 2011

“አህባሽ” ሆይ! የሱስንዮስና የአጼ ዮሀንስ ዘመን አልፏል!


Ubah Abdusalam
የኢትዮጵያ ታሪክ በጦርነትና በፍትጊያ የተሞላ ነው፡፡ ከነዚህ ጦርነቶች መካከል አብዛኛዎቹ በእብሪተኛ መሪዎች ቀስቃሽነት ነበር የተካሄዱት፡፡ ዓለም በስልጣኔና ጎዳና ወደ ፊት ሲገሰግስ የያኔዎቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ግን “እኔ አውቅልሀለሁ” በሚል ጀብደኝነታቸው ህዝቡን እርስ በራሱ ያጫርሱት ነበር፡፡ አንዳንድ መሪዎችማ ህዝቡ የቀድሞ እምነቱን ትቶ እነርሱ የመረጡለትን ጎዳና እንዲከተል ለማስገደድ ሲሉ ህዝቡን ከፍተኛ እልቂት ባስከተሉ ጦርነቶች ውስጥ ሲዘፍቁት ኖረዋል፡፡ ነገር ግን እነርሱ የፈለጉት ሃይማኖትን የማስቀየር ፖሊሲ አልተሳካላቸውም፡፡ ይህንንም በሁለት ምሳሌዎች መግለጽ ይቻላል፡፡ 
  •   አጼ ሱስንዮስ (ከ1605-1632)፡- አጼ ሱስንዮስ ከምዕራብ አውሮፓ (ፖርቱጋልና እስፔን) በመጡት የካቶሊክ እምነት ሰባኪያን ተማርኮ ሃይማኖቱን ለወጠ፡፡ ሳይውል ሳያድርም በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ካህናት፤ ቀሳውስትና መላው የክርስቲያን ህዝብ የኦርቶዶክስ ሃይማኖቱን ትቶ ወደ ካቶሊክ እምነት እንዲገባ አዋጅ አስነገረ፡፡ ህዝቡ ግን ትዕዛዙን “አልቀበልም!” አለ፡፡ በነገሩ የተናደደው አጼም ፍላጎቱን በሃይል ለመፈጸም ተነሳ፡፡ መላው ሰራዊቱን በክርስቲያኑ ህዝብ ላይ አዘመተ፡፡ ህዝቡም ከሱስንዮስ ሰራዊት ጋር ተጋፈጠ፡፡ በሀገሪቱ ላይ የጦርነት እሳት ነደደ፡፡
  አጼ ሱስንዮስ ጀብደኝነት ባሳወረው ወኔው በጦርነቱ ገፋበት፡፡ ለ27 አመታት በዘለቀው የስልጣን ዘመኑ ምንም ሳይሰራበት ሀገሪቷን በጦርነት እሳት ሲለበልባት ቆየ፡፡ እርሱ የለኮሰው እሳት የቆመው አጼው “አለም በቃኝ” ብሎ ወደ ገዳም ሲገባና ልጁ ፋሲል በአባቱ ቦታ ንጉስ ተብሎ ሲሾም ነው፡፡
(ይህ ምሳሌ የሚመለከተው ክርስቲያኖችን ነው፡፡ ቢሆንም ክርስቲያን ወገኖቻችን አሁን እኛን የገጠመን ፈተና በሱስንዮስ ዘመን ያጋጠማቸውን ፈተና ያህል ከባድ እንደሆነ እንዲረዱልን ስለምፈልግ በምሳሌነት ጠቅሼዋለሁ)፡፡ 
  • አጼ ዮሀንስ አራተኛ (ከ1870-1888)፡ አጼ ዮሀንስ “በአንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት” በሚለው ፖሊሲያቸው ይታወቃሉ፡፡ ይህንን ፖሊሲ በስራ ላይ ለማዋል ሲሉ ከታናሻቸው ከምኒልክ ጋር እንኳ ተጣልተዋል (ምኒልክ ጥሩ ባይባሉም በሃይማኖት ፖሊሲያቸው ከዮሀንስ ይሻላሉ)፡፡
አጼ ዮሀንስ ፖሊሲያቸውን ለመተግበር ሲነሱ በቅድሚያ የመረጡት የወሎ ክፍለ ሀገርን ነው፡፡ በዚሁ መሰረትም ለብዙ ምዕተ አመታት እምነታቸውን አስጠብቀው የቆዩት የወሎ ሙስሊሞች በአንድ ወር ውስጥ ክርስትና ካልተነሱ በሰይፍ እንደሚቀጡ አዋጅ ተነገረ፡፡
ወላዋዩና ሹመት ፈላጊው (እንደ ራስ ሚካኤል አይነቱ) የአጼውን ትእዛዝ ለመፈጸም ተሸቀዳደመ፡፡ አብዛኛው ህዝብ ግን እስልምናን በምንም ዋጋ እንደማይለውጥ ለአጼው ቁርጡን ነገራቸው፡፡ በነገሩ የተናደዱት አጼ ዮሀንስ የሽብርና የጦርነት ጅራፋቸውን በወሎ ህዝብ ላይ መዘዙ፡፡ ሙስሊሙ ህዝብ በሼኽ ጠለሃ ጃዕፈር፤ በአብደላ ጪፍራ፤ በአባ ዋጠው እና በሌሎችም ሙጃሂዶች ዙሪያ በመሰለፍ እብሪተኛውን አጼ ተጋፈጠ፡፡ የአጼው ጥቃት እየባሰበት ሲሄድም ሙስሊሙ ህዝብ ለሃይማኖቱ ሲል ወደ ሀረር፤ ባሌ፤ ጅማ እና ጉራጌ ተሰደደ፡፡ ነገሩ አንጀቱን ያሳረረው ደግሞ ወደ ሱዳን እተሰደደ ከኢማም አህመድ አልማህዲ ጦር ጋር ተቀላቀለ፡፡
አጼው በጦርነት ፖሊሲያቸው ገፉበት፡፡ ሆኖም ጦርነቱ ሃይማኖትን ሊያስለውጥ አልቻልም፡፡ እንዲያውም የርሳቸው ህይወት እንዲቀጠፍ ምክንያት ሆነ፡፡
ከላይ የጠቀስናቸው ሁለት ምሳሌዎች በርካታ ቁምነገሮችን ያስተምሩናል፡፡ ምሳሌዎቹን በትክክለኛ አእምሮ ያነበበ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ እምነትን በግድ ለመጫን የሚደረግ ጥረት መጨረሻው ውድቀት እንደሆነ በደንብ ይገነዘባል፡፡
ዛሬ አለም በሰለጠነበትና ጭፍንነትና አጉል አክራሪነት አንድ እርምጃ እንኳበማያራምዱበት ዘመን አህባሾች “አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ” ሊሉን መጥተዋል፡፡ ከኋላቸው በሚገፋቸው ስውር እጅ (አሜሪካ) እየታገዙ የመጅሊስን ስልጣን በመቆጣጠራቸው ብቻ ድል የሚቀናቸው እየመሰላቸው ነው፡፡ ህዝቡ ግን “እስከዛሬ የተከለተላችሁት እምነት ስህተት ስለሆነ በአዲስ መልክ ወደ እስልምና ግቡ” ሊሉት የመጡ መሆናቸውን በደንብ ያውቃል፡፡ የዓለም ህዝብ የሚያምንባቸውንና ለሃይማኖታቸው ከልባቸው ሲሰሩ የቆዩትን ኡለማ “ካፊር ናቸው” እያሉ በመሳደባቸው ብቻ ልቡ ቆስሏል፡፡
ስለዚህ አህባሾች የመጅሊስን ስልጣን ቀርቶ የሀገሪቱን ስልጣን ሙሉ በሙሉ ቢቆጣጠሩ እንኳ የሚለውጡት አማኝ ያለ አይመስለኝም፡፡ ይህ ህዝብ አያቶቹ ከነ አጼ ዮሐንስ ጋር እየተጋፈጡ የጠበቁትን እስልምና በተራ ጮሌነት ያስረክባል ብለው ገምተው ከሆነ በህልም አለም ውስጥ ነው ያሉትና ህዝቡ ራሱ “ከህልማችሁ ንቁ!”ይላቸዋል፡፡ እውነታው ደግሞ በተግባር ይታያል፡፡
ድል የኢስላም ነው!! አላሁ አክበር!!

Monday, October 17, 2011

“አህባሽ”፤ ዴቪድ ሺን እና የኢትዮጵያ የሙስሊሞች ስጋት

Ubah Abdusalam Seid

“የአህባሽ” ጀመዓ ለብዙዎቻችን ስጋት ከሆነባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ የአንጃው አመለካከቱን በህዝቡ ውስጥ ለማስረጽ ሲል ከጸረ-እስላም ሃይሎች ጋር እንኳአንድ ላይ ወግኖ ሙስሊሞችን ከመጉዳት ወደ ኋላ የማይል መሆኑ ነው፡፡ የአንጃውን የኋላ ታሪክ የሚያውቁ ወገኖች ይህንን በስፋት ሲዘረዝሩ ነበር፡፡ ለመሆኑ ይህ ጽንፈኛ አንጃ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ሙስሊሞችን እንዲመራ ማን መረጠው?
ይህን ጥያቄ መመለስ ይከብዳል፡፡ ሆኖም አንድ ነገር በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ጉዳይ ለብቻው አልወሰነውም፡፡ ነገሩ የበርካቶች እጅ አለበት፡፡ ከሁሉም እጆች የሚተልቀው ደግሞ የአሜሪካ እጅ ይመስለኛል፡፡
አሜሪካ ከመስከረም 11/2011 ወዲህ በሽብር ላይ ጦርነት ከፍቻለሁ ትላለች፡፡ ቀንደኛ አሸባሪዎችን የሚፈለፍለውም “እስላማዊ አክራሪነት ነው” ባይ ነች፡፡ በአሜሪካ አመለካከት “የእስላማዊ አክራሪነት ምንጭ “ወሃቢያ” የሚባለው ቡድን ነው፡ ኢትዮጵያም ወሃቢያ እየተጠናከረ የመጣባት ሀገር ናት፡፡ ስለዚህ የወሃቢያን አክራሪ አቋም ለመቆጣጠር በርካታ ዘዴዎችን መጠቀም ያፈልጋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ  ከሙስሊሞች መካከል ከወሀቢያ ጋር ፈጽሞ የተቃረነ ትምህርትና የእምነት ፍልስፍና ያላቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች ማጠናከርና በወሃቢያ ላይ የበላይ እንዲሆኑ መርዳት ነው፡፡” በዚህ ስሌት መሰረት ነው እንግዲህ “አህባሽ” በአለም አቀፍ ደረጃ የተመረጠልን፡፡ ለመሆኑ ይህንን ጥቆማ ለአሜሪካ የሰጠው ማን ነው?
ብዙዎች አህባሽን “ለኢትዮጵያ የመረጡት ፕሮፌሰር ሀጋይ ኤርሊች ናቸው” ይላሉ፡፡ እኔ ግን ሀጋይ ኤርሊችን ብቻ አልጠረጥርም፡፡ ከሀጋይ ኤርሊች በላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩትን ዴቪድ ሺንን እጥረጥራለሁ፡፡ ምክንያቱም ሃጋይ ኤርሊች ነገሩን በይፋ በማቀንቀን የመጀመሪያ ሰው ይሁኑ እንጂ አህባሽ በኢትዮጵ ውስጥ ቢናጠከር ለኢትዮጵያም ሆነ ለአሜሪካ ጥቅም የሚበጅ እንደሆነ  በፖሊሲ ደረጃ ሲሰብኩ የነበሩት ዲቪድ ሺን ነበሩ፡፡ ለዚህም አምባሳደር ዴቪድ ሺን በዲሴምበር 20/2004 ቤይሩት በሚገኘው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ (American University of Beirut) “እስልምናና ግጭቶች በአፍሪካ ቀንድ?” በሚል ርዕስ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ ግንባር ቀደም ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ (የዴቪድ ሺንን ጽሁፍ ከሚቀጥለው ዌብሳይት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ጽሁፉ ሰፊ ስለሆነ ከቻላችሁ ሁሉንም አንብቡት፡፡ ካልቻላችሁ እኛን የሚመለከተውን ክፍል ብቻ አንብቡ፡፡ http://www.ephrem.org/dehai_archive/2005/nov04-jan05/0562.html  )
ዲቪድ ሺን ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ በርካታ የፖሊሲ ጥናቶችን አቅርበዋል፡፡ ይህ ጽሁፋቸው ግን “አህባሽ በአሜሪካ መንገድ ላይ ይለፍ” የሚለውን አረንጓዴ መብራት ያበራ እንደሆነ ከአቀራረቡ መረዳት ይቻላል፡፡
ዲቪድ ሺን ከሰባት ዓመት በፊት የተነፈሱት የፖሊሲ ሀሳብ በሙከራ ደረጃ በስራ ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ ለዚህም አንዳንድ መረጃዎችን ልስጣችሁ፡፡
  1. የአሜሪካ ኤምባሲ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲያዘጋጃቸው የነበሩት የረመዳን የኢፍጣር ፕሮግራሞች (በዚህ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙ ሲጋበዙ የነበሩት እነማን ናቸው? እንዴትስ ነው የሚመረጡት? ) 
  2. አሜሪካ በራሷ በጀት በባሌ የሚገኘውን የዲሬ ሼኽ ሁሴን መስጊድና የመቃብር ቦታ ማሰደሷ(አሜሪካ “ወሃቢዎች ዲሬ ሼኽ ሁሴን የመሳሰሉትን ቀደምት መስጊዶችና የመቃብር ቦታዎች ማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ ሱፊዎች የሚጎበኟቸውን የመቃብር ቦታዎችና ሀድራዎች ማጠናከር ያስፈልጋል” ትላለች፡፡) 
  3.  ባለፉት ሁለት ዓመታት በተካሄዱት የመጅሊስ ምርጫዎች “ወሀቢዎች” እስከ ወረዳ ድረስ ባለው ባሉት ኮሚቴዎች እንዳይሳተፉ በሚል ሰበብ ሲሰሩ የነበት የምርጫ ቲያትሮች
ነገሩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በትጋት ሲካሄድ ነበር፡፡ ይህንንም አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ በጻፉትና ዊኪሊክስ በኢንተርኔት በለቀቀው የቴሌግራም ዘገባ በስፋት ነግረውናል፡፡ (ቴሌግራሙን ለማንበብ የሚቀጥለውን የዊኪሊክስ ገጽ ይክፈቱ http://wikileaks.org/cable/2009/07/09ADDISABABA1674.html )
የሚገርመው ነገር የትኛውም የአህባሽ ጀመዓ አባል ይህንን ጉዳይ የማያስተባብል መሆኑ ነው፡፡ እንደ አህባሾች አመለካከት “ወሀቢያ የተባለው ቡድን እስልምናን ለማጥፋት በሙሉ ሃይሉ የሚሰራ የሙናፊቆች ስብስብ ነው፡፡ ስለዚህ እርሱን በተቻለው መንገድ ሁሉ መታገል ያስፈልጋል፡፡” አህባሾች በቀጥታ የሚሉት ይህንን ነው፡፡
ታዲያ ምን ይዋጠን! “አህባሽ” ስለማንቀበለው ብቻ በተለመደው ጽንፈኛነቱ “ወሃቢያ ናችሁ!” ይለናል፡፡ አሁንማ “ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች” አይነት ነገር ሆኖብናል፡፡ አሜሪካን ተጠግቶ እኛን ሊፈራ?አላህን ያልፈራ እኛን እንዴት ይፈራል!
ስለዚህ ከሰሞኑ ስጋታችን በጣም ጨምሯል፡፡ በአሜሪካ አጋፋሪነት ስለ “ወሃቢያ” እና ስለ “ሱፊያ” በጥልቀት የማያውቀውን የኢትዮጵያ መንግስት አሳስቶ ጉድ እንዳይሰራን ብቻ!! ከሰሞኑ ግር ግር እንደማየውማ “ወሃቢያ ናችሁ” በሚል የጸረ-አሸባሪነት ህግ የሚባለውን አሳሳቢ አዋጅ በሙስሊሞች ላይ እያስመዘዘ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ለስቃይ እና ለእንግልት እንዳይዳርግ ያሰጋናል፡፡ ስለዚህ ስጋታችን “ስጋት” ብቻ ሆኖ እንዲቀር ትግላችንን በዚህ አቅጣጫ መቀየስ የሚገባ ይመስለኝ፡፡
ያ ጀመዓ! እኔ ይህንን ብያለሁ፡፡ እናንተስ ምን ትላላችሁ? አህባሽ “አህሉ ሱንና ወልጀመዓ” የሚለውን ስም በውሸት ደርቦ “ወሃቢ ናችሁ” እያለ የፈለገውን ሊፈጽምና ሊያስፈጽም አሰፍስፏል፡፡እርሱን በመመከቱ ዙሪያ በጋራ እንወያይ፡፡ ሀቅን እስከያዝን ድረስ የአላህ እርዳታ ከኛ ጋር ነው፡፡
በሉ ሀሳብ ስጡ ያ ጀመዓ!!
ወሰላሙ ዓሌይኩም ወራህመቱላህ!!



Ahbash-West Connection: Who is their enemy, the “Wahhabiyya” or Islam itself?

By Ubah Abdusalam Seid
Tracing to the background of its founder (Sheikh Abdullah Al-Harari) and its inner interest, I wondered why the group called “Ahbash” blaspheme and curse Muslim revivalists such as Sayyid Qutb, Rashid Rida, Jamaluudin Al-Afghani and their followers. I say this because in the teachings of these Islamic revivalists, you can’t see a direct clash with the tenets of Ahbashi’s interests (remember that Ahbash’s main interest is to protect their own version of Islam which is highly mixed with polytheism/shirk and superstition).  They don’t emphasize “Aqidah” or what nullifies one’s Aqidah. In their writings, they also don’t mention about “grave worshiping” to which the “Ahbash” are highly symphatic. It’s really confusing to know the reason. But as you study the Ahbashi’s inclination to the secularists and especially to the western governments, you would know the reason. I state it according to a minor study of mine.
For long years, the westerns were searching a group which marches against “Militant Islamism” (in the western words) from within Islam itself. They found that “Ahbash” is against the formation of Islamic state (in any form, be in a Caliphate form or an Islamic Republic). Further, they learned that “Ahbash” doesn’t allow Muslims to participate in politics and form a political party. They assed the case from different angles and they are satisfied when they realized the “Ahbash” objective is to form moderate Muslims who hold Islam to the minimum. That is, for Ahbash, it’s enough to say “great achievement” if they create a Muslim who hold his religion only for ceremonial purposes- for example a Muslims who goes to the mosque only on Jum’a/Friday and in Ramadan .
The westerns, as heard its emergence and approached it in Beirut in 1980- early 1990s, were very delighted by the stand of Ahbash. But it was hard for them to split it from Syria (Ahbash’s patron state at the time). Latter, as the Hezbollah was growing higher, Syria started to neglect Ahbash and turn its face to Hezbollah. So the poor Ahbash lost its ground and rush to take refuge to the west. It was accepted warmly and equipped with what it needed (I think the staff of the American University of Beirut served to form this West-Ahbash negotiations). The Ahbash then, to make the westerns please more, starts blaspheming past scholars whom it thought “the architects of militant Islamism”. The story goes then, and with the September 11/2001 attacks, Ahbash got the greatest chance where it would have to win a big trophy from the west for being “the true Muslims who can live with west in the future world”. This was the clue as to why Sayyid Qutb and other revivalists became the chief enemies of Ahbash jama’a in addition to their old enemies like Sheikhul Islam ibn Teymiyyah and Sheikh Muhammad ibn Abdul-Wahhab.
So, I definitely believe that the rumor of “Ahbash-west connection” is not only a rumor. It’s one piece of the group’s involvement in multi million conspiracy projects. The target is not to demolish the group called “Wahhabiya” whom the west and “Ahbash” accused as “the proponents of Militant Islam”.  But it is Islam itself.
Today, what makes us sad is not the enmity of the west. It is Ahbash’s being the only groups who call themselves “Muslim” but serve the western interests. Since the westerns singled out Islam as their “fierce enemy”, the Muslims of the world (both Sunni and Shi’a) have come close to each other to voice against the aggressors. But “Ahbash” is entering to all Muslim communities and making them to fight each other, then through, fulfilling the interest of the west. The Ahbashi’s dictation of the word “Wahhabiya… Wahabiyya…” has no other objective except serving the interest of the west and keeping their version of Islam in place. So what is the solution?
Allah knows the solution but be sure that He protects His religion and His Party (Muslims).