Wednesday, May 16, 2012

አህባሽና ጽዮናዊው Anti Defamation League

ኡባህ አብዱሰላም ሰኢድ
  
“አህባሽ” በሙስሊሙ ዓለም አነጋገሪ የሆነበት አንደኛው ምክንያት “አንጃው ለጽዮናዊያን ሀይለኛ ፍቅር አለው” ተብሎ መነገሩ ነው፡፡ በርግጥም አህባሽ ከጽዮናዊያን ጋር ሞቅ ያለ ፍቅር እንዳለው የሚያስረዳው ትልቁ ነገር ድርጊቱ ነው፡፡ የአንጃው ጽሁፎች፤ ፕሮፓጋንዳዎችና ድርጊቶች በሙሉ ጽዮናዊያን በሚፈልጉት ስልት የተቃኘ ነው፡፡ ስብከቱ፣ ተረቱ፤ ውረፋው፤ ጥላቻው፤ ወዘተ… ያነጣጠረው በሙስሊሞች ላይ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ባህሪ ነው የጽዮናዊያንን አንጀት የሚያርሰው፡፡
ሆኖም እስከዛሬ ድረስ ይህንን ጉዳይ በተሟላ ሁኔታ የሚያጠናክርልን ማስረጃ ለማግኘት ተስኖን ቆይቷል፡፡ ከሀገራችን ጉዳይ ጋር አያይዘን እንደ ትልቅ ማስረጃ የምናቀርበው የጽዮናዊውን ፕሮፌሰር የሀጋይ ኤርሊችን ጽሁፎች ነው፡፡ በርግጥም ሀጋይ ኤርሊች “አህባሽ”ን ለመሪነት ካጩልን ሰዎች መካከል ቀንደኛው ነው፡፡ ከዚያ ባለፈ ግን ነገሩን በእርግጠኝነት የምናስረዳበት ማስረጃ አልነበረንም፡፡
ዛሬ ግን (ጥቅምት 14/2004) ተሳክቶልናል። አልሐምዱሊላህ! የመጀመሪያው ትልቅ ማስረጃ ከእጃችን ገብቷል፡፡ ይህ ማስረጃ አህባሾች በፌስቡክ ቡድናቸውና በመርከዛቸው “ተረት ነው፤ አሉባልታ ነው፤ የጠላት ወሬ ነው!...” ወዘተ እያሉ በማጭበርበር ነገሮችን እንዲሸፋፍኑ እድል የማይሰጣቸው አይነት ነው፡፡ በዚህ በኩል ጥሩ ነው፡፡ በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእምነት ነጻነት ላይ የተደቀነውን ታላቅ አደጋ የሚጠቁም በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት ይቀሰቅሳል፡፡
ለማንኛውም ማስረጃውን እነግራችኋለሁ፡፡ ከዚያ በፊት አላህ ይህንን ውድና ጠቃሚ የሆነ ማስረጃ በእጃችን ላይ ስለጣለልን ምስጋናችን ይድረሰው እላለሁ፡፡ በማስከተልም ይህንን ውድ ማስረጃ ያመጡልንን “የጸረ-አህባሽ” ፌስቡክ ቡድን መስራች አባላትና መሪዎች “አላህ ምንዳቸውን ያብዛው፤ ከክፉ ነገር ይጠብቃቸው” ለማለት እወዳለሁ (እናንተም ዱዓ አድርጉላቸው)፡፡
የጸረ- ስም ማጥፋት ሊግ (Anti-Defamation League)
እንደዚህ የሚባል ድርጅት ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? እኔ ግን እስከ እሁድ ሌሊት (ጥቅምት 14/ 2004 ዓ.ል.) ድረስ በዚህ ስም የሚጠራ ድርጅት ስለመኖሩ በጭራሽ ሰምቼ አላውቅም፡፡ የሚገርመው ታዲያ ድርጅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ “ሰብአዊ መብትን እናስጠብቃለን” በሚል ስም ከተቋቋሙ ጥንታዊ ተቋማት ጋር የሚመደብ መሆኑ ነው፡፡ ከፍልስጥኤማዊያን ጥያቄ  ጋር በተያያዘ በአል-ጀዚራና በሌሎችም ጣቢያዎች በየጊዜው አስፈሪ ዘገባዎች የሚቀርቡበት ድርጅት መሆኑም ሌላ ነገር ነው፡፡ የድርጅቱ ዌብሳይት እልፍ አእላፍ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከሚያዘወትሯቸው ድረ-ገጾች መካከል የሚመደብ መሆኑም ሌላ የማላውቀው እንቆቅልሽ ነው፡፡ በአጭሩ “የኢንተርኔት ሱሰኛ ነኝ” እያልኩ ስጀነን ኖሬ እንዲህ ዓይነት ስመ-ገናና ድርጅት መኖሩን እንኳ አለማወቄ “በጣም ገና” ከሚባሉት ጀማሪዎች ጎራ ውስጥ የምመደብ መሆኑን አሳይቶኛል፡፡ 
“የጸረ-ስም ማጥፋት ሊግ” ዓላማው፣ ስያሜውና ድርጊቶቹ ሶስቱም ይለያያሉ፡፡ የድርጅቱን ዌብሳይት ስትከፍቱ ዓይናችሁ በቅድሚያ የሚያርፈው “to stop the defamation of the Jewish people: To secure Justice and fair treatment for all” ተብሎ በተጻፈው የድርጅቱ ዓላማ ማስተዋወቂያ ላይ ነው (በአማርኛ “በአይሁዶች ላይ የሚካሄደውን ስም ማጥፋት ማስቆም- ፍትሃዊነትና እኩልነትን ለሁሉም እንዲሆን ማረጋገጥ” እንደማለት ነው)፡፡ ይህንን መፈክር እንደ አላማ አድርጎ የሚጠቀመው የዚህ ድርጅት ዋነኛ ተግባር ግን “ጽዮናዊነትን ማጠናከርና የእስራኤልን ዘረኝነትና ተስፋፊነት በአለም ዙሪያ ማስተጋባት ነው”፡፡ (ለማስረጃው የሚቀጥለውን የድርጅቱን የኢንተርኔት አድራሻ ከፍታችሁ ተመልከቱ www.adl.org )
Anti-Defamation League (ADL) በ1913 በአሜሪካ ውስጥ የተቋቋመ አይሁዳዊ ተቋም ነው፡፡ በአሜሪካ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ምህዋሮች ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ ካላቸው ግዙፍ ተቋማት መካከልም አንዱ ነው፡፡ ሊጉ በአሜሪካ ውስጥ ካሉት ከሰላሳ በላይ ቅርንጫፎች በተጨማሪ አይሁዶች በሚበዙባቸው ሶስት ሀገራት ውስጥም (እስራኤል፤ ሩሲያና ኢጣሊያ) ውስጥ በይፋ ይንቀሳቀሳል፡፡
ADL “ዋነኛው ዓላማዬ አይሁዶችን ከጥላቻ መታደግ ነው” ይላል፡፡ የጥላቻ ጥቃቶች በሌሎች የብሄረሰብና የእምነት ቡድኖች ላይ እንዳይደርሱ ለመከላከል በሚል በርካታ እንቅስቃሴዎችንም እንደሚያደርግ ይገልጻል፡፡ ድርጅቱን ከ“ሀ” እስከ “ፐ” የሚያውቁ ወገኖች ግን የድርጅቱን መሰሪነት ነው የሚናገሩት፡፡ እኒህ ወገኖች እንደሚሉት “ADL” ፀረ-ሴማዊነትን (ጸረ-አይሁድ አስተሳሰብን) ለማጥፋት በሚል ሽፋን “ሴማዊነት”ን (የአይሄድ የበላይነትን) በሁሉም ህዝቦች ላይ ለመጫን ሌት ተቀን የሚሰራ ጽዮናዊ ድርጅት ነው፡፡ በተለይ በእስራኤል መንግስት ህገወጥ ተግባራት ላይ ትችት የሚያቀርቡ ግለሰቦች፤ መንግስታትና ድርጅቶችን “ጸረ-ሴማዊ” እያለ ማጥላላት፣ ማንጓጠጥ፣ ማስፈራራትና “ጽንፈኛ”፣ “አክራሪ”፣ “አሸባሪ” የመሳሰሉ ቅጽሎችን መስጠት ቀዳሚ ተግባራቱ እንደሆኑ ያብራራሉ፡፡
ADL ፍልስጥኤማዊያንን ለሚረዳ ማንኛውም ተቋምና ግለሰብ ምህረት የለውም፡፡ የተባበሩት መንግስታት በእስራኤል ላይ እርምጃ ለመውሰድ ቀጠሮ ሲይዝ ADL በጓሮ በር ወደ “ዋይት ሀውስ” ይገባና “እስራኤል ማለት አሜሪካ ማለት ናት፡፡ ስለዚህ የቬቶው ነገር እንዳይረሳ!” በማለት ቀጭን ማስታወሻ ያስነግራል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለፍልስጥማዊያን ተጨቋኞች የሞራል ድጋፋቸውን ለመግለጽ ስብሰባ ሲጠሩ ADL የየተቋማቱን ዲኖች በስልክ ይገናኝና “ዋ! እንዲህ አይነት ስብሰባ በግቢያችሁ ቢካሄድ ከሚቀጥለው ሴሚስተር ጀምሮ የፌዴራሉ መንግስት ለትምህርት ተቋማት የሚልከው ድጎማ ይቋረጥብሀል” የሚል ሽብር ነዝቶ ስብሰባዎቹን ያሰናክላል፡፡
“ADL” ሽብርተኝነትና ጽፈኝነትን ከሩቁ የማሽተት ሀይል አለኝ ባይ ነው፡፡ በመሆኑም “በጽንፈኝነት” ዙሪያ የአሜሪካ መንግስትን ያማክራል፡፡ በመረጃ ቋቱ (data base) ውስጥ “ጽንፈኛ”፤ “አሸባሪ”፤ “ጸረ-ሴማዊ” ወዘተ… የሚሉ ታርጋዎችን የለጠፈላቸውን የበርካታ ግለሰቦችና ድርጅቶችን ዝርዝር መረጃ አከማችቷል፡፡ በጸረ-ሴማዊነት ጥርሳቸውን የነከሰባቸውን ሰዎች ንግግርና ድርጊት እየተከታተለ ይቀርጽና ከመረጃ ቋቱ ውስጥ መዝግቦ ያስቀምጣል፡፡ ከነዚህ ግለሰቦች መካከል ለአንዳንዶቹ ስም የማውጣቱን ስራ አጠናቋል፡፡ የሚጠብቀው ሰዎቹን ለቃቅሞ ቂሙን የሚወጣበትን አጋጣሚ ብቻ ነው፡፡ ከነርሱ መካከል አንዳንዶቹ በማስሚዲያ የምናውቃቸው ስሞች በመሆናቸው ብዙም አያስደንቁም፡፡ ነገር ግን “ADL” ለኛ በይፋ ላልተነገሩን በርካታ ግለሰቦችና ተቋማትም የጽንፈኝነት ታርጋ እየለጠፈ በመረጃ ቋቱ ውስጥ መዝግቦአቸዋል፡፡ ለምሳሌ ታዋቂው ሙፍቲ “ዶ/ር ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ” በዚህ ጽዮናዊ ድርጅት “Theologian of Teror” ተብለው ተመዝግበዋል፡፡ (ለዝርዝሩ ይህንን ገጽ ይክፈቱ http://www.adl.org/main_Arab_World/al_Qaradawi))
ባጠቃላይ ከላይ የገለጽኩት የአሜሪካዊው ADL ሁለመናው ጽዮናዊነት ነው፡፡ “ጽዮን.. እየሩሳሌም.. አንቺን ከረሳሁ.. ዳዊት ይርሳኝ…” አይነት ነገር ነው፡፡(አላህ ያጥፋው አቦ! ይሄ ሰላቢ!!)፡

ADL እና ጉደኛው “አህባሽ”
አሁን ከዋናው ነጥባችን ላይ ደርሰናል፡፡
ዛሬ ባቀረብኩላችሁ ጽሁፍ ገኖ የዋለው ADL በአካል ከኛ ርቆ ነው ያለው፡፡ የጽዮናዊነት ንቅናቄውንም ከኛ በሚርቁ ሀገራት ውስጥ ነው የሚካሄደው፡፡ ስለዚህ አጀንዳችን ሊሆን ባልተገባ ነበር፡፡ የኛ አጀንዳ ሆኖ ቢገኝስ ምን ትሉ ይሆን?
ወገኖቼ! በርግጥም በአህባሽ ምክንያት ADL የኛም ስጋት ሆኗል፡፡ ከማንም ጋር “እሸሼ ገዳሜ” ሲል የኖረውና የጽንፈኞች ጽንፈኛ የሆነው “አህባሽ” በጽዮናዊው ADL ስር በማህበርተኝነት ከታቀፉት አባል ድርጅቶች አንዱ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ሁለቱ የፌስቡክ ቡድናችን አባላት የዛሬ ሶስት ወር ገደማ ያጋለጡት ይህንን አስደናቂ ሚስጢር ነው፡፡ በህይወቴ እንደዚህ አይነት አስደናቂ ነገር ሲገጥመኝ ለሶስተኛ፤ ወይም ለአራተኛ፤ ወይም ለአምስተኛ ጊዜ ቢሆን ነው (ተጋነነ እንዳይባል ስለሰጋሁ ነው እንጂ በሶስተኛ ላይ ማቆም ይቻል ነበር)፡፡
“አህባሽ” በጣም ወራዳና አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን “ርካሽና ዝቃጭ” ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ የበለጠ ውርደት ከየት ይመጣ ይሆን? ይህንን ውርደት ለማየት የሚሻ ሰው የሚቀጥለውን ድረ-ገጽ ይመልከት፡፡ አህባሽን በጽዮናዊው ADL የፊላደልፊያ ቅርንጫፍ ቢሮ ስር ከተመዘገቡት ማህበርተኞች መካከል አንዱ ሆኖ ያገኘዋል፡፡  http://www.adl.org/philadelphia/coalition.asp
ከዝርዝሩ እንደምትረዱት
·        አህባሽ Association of Islamic Charitable Projects በሚለው የእንግሊዝኛ ስሙ በአራተኛ ተራ ቁጥር ተመዝግቦ ይታያል። (ዝርዝሩ በእንግሊዝኛ ፈደላት ቅደም ተከተል የተጻፈ መሆኑን ልብ በሉ)።
·        “ሙስሊም ማለት እኔ ብቻ ነኝ” እያለ በሙስሊሞች ላይ ተክፊር ከሚያውጀው “አሕባሽ” በስተቀር “ሙስሊም” ነኝ የሚል አንድም ድርጅት በዝርዝሩ ላይ የለም፡፡ ወላ ሱኒ! ወላ ሺዓ ማፊሽ! ሌላው ቀርቶ በኑፋቄ አቀንቃኝነታቸው የሚታወቁት የአህመዲያ ፊርቃ እነ የጥቁር አሜሪካዉያኑ Nation of Islam እንኳ በዝርዝሩ ላይ የሉም፡፡ አስተግፊሩላህ!!!፡፡
·        ከክርስትናው በኩልም "Metropolitan Christian Council of Philadelphia" ከተባለ ድርጅት በስተቀር ሌላ የክርስቲያኖች ቡድን የለም፡፡ አንድ ወንድማችን እንደጻፈው ይህኛው ድርጅት ጽዮናዊያን  ለክርስቲያኖቹ የሰሩት ሌላኛው “አህባሽ” ሳይሆን አይቀርም ብለን ጠርጥረናል፡፡
·        ከሁሉም የሚያስገርመው ለግብረ-ሰዶማዊያንና ለሴት ለሴት ጋብቻ መብት እንታገላለን የሚሉ ሁለት ድርጅቶችም በዝርዝሩ ላይ ያሉ መሆናቸው ነው፡፡
የአህባሽን ቅሌት አይታችሁታል አይደል? ሰልፉ የጽዮናዊያን ብቻ አይደለም፡፡ ሌሎች ወራዳዎችና ዝቃጮችም በጥምረቱ ውስጥ አሉ፡፡ የግብረ- ሰዶማዊያን መብት አስከባሪዎች!
ወርደት! ውርደት! እጅግ በጣም አሳፋሪ ውርደት! የግብረ-ሰዶማዊያንን” መብት እናስከብራለን ከሚሉ ድርጅቶች ጋር መሰለፍ ማለት ምን ማለት ነው? እስላማዊ ነኝ የሚል ድርጅት እንዲህ አይነት ነገር ይሰራል? የትኛው የቁርአን አያህ ነው ይህንን የሚፈቅደው? በየትኛው ሀዲስ ነው ይህ የተፈቀደው? አስተግፊሩላህ! እፍረት! እፍረት! ትልቅ እፍረት!!! ያ ረቢ ኢስቱርና! ኻቲማችንን አብጀው!
ጽዮናዊው ADL ሌሎችን ለማደናገር የፈለገ ይመስል አህባሽ የተሰለፈበትን ጥምረት No Hate Project ብሎታል፡፡ “ጥላቻ በኛ መሀል የለም” ለማለት ነው፡፡ በእውነትም ጥላቻ በነርሱ መሀል የለም፡፡ በኛና በነርሱ መሀል ግን ከንግዲህ ወዲህ እርቅ የለም፡፡ ከእንዲህ አይነቱ ወራዳ ድርጅት ጋር የሚደራደር ሙስሊም ከእንግዲህ ወዲህ የለም፡፡
ድል የኢስላም ነው፡፡


  

No comments:

Post a Comment