Thursday, May 17, 2012

አህባሽ እና “ሺዓ“


ኡባህ አብዱሰላም ሰኢድ
   
 በዚህ ጽሁፍ የአህባሽን ነገር ከሺዓ ጋር እያነጻጸርኩ እንድናየው ፈለግኩ፡፡ ከዚያ በፊት አንድ ነገር ልናገር፡፡
   አንዳንድ ሰዎች ይህንን ርዕስ ሲያዩሁለቱም ጠማሞች ናቸው፤ ለምን ስለነርሱ መጻፍ አስፈለገማለታቸው አይቀርም፡፡ የኔም አላማ ከሁለቱ አንዱን ለወዳጅነት እንድንመርጥ መገፋፋት አይደለም፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ የተነሳሳሁት አንዳንድ የፌስቡክ ጓደኞቼ አህባሽን ከሺዓ ጋር ሲያመሳስሉ በማየቴ አባላላቸው ስህተት መሆኑን ለማስረዳት ነው፡፡ ለዚህም የሁለቱን መመሳሰልና ልዩነታቸውን አብረን እናያለን፡፡
የአህባሽና የሺዓ መመሳሰል
   አህባሽ የሚባለው አንጃ እና የሺዓ ሙስሊሞች በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ተመሳሳይ (ተቀራራቢ) አቋም አላቸው፡፡
1.      ሰሞኑን እንዳየነው አህባሾች ስለተወሱልእናተበሩክበሀይለኛ ሁኔታ ይከራከራሉ፡፡ ሺዓዎችም በዚህ ላይ ተቀራራቢ አቋም አላቸው፡፡ ነገር ግን ሺዓዎች ለተወሱልና ለተበሩክ የሚመርጡትአውሊያከአህሉል በይት (የፋጢማ ዛህራ እና የአሊ ኢብን አቡጣሊብ የዘር ሀረግ የተገኘ) መሆን አለበት ይላሉ፡፡
2.     አህባሾችበአውሊያ መቃብር ላይ ደሪህ መገንባትና መቃብሮችን ዚያራ ማድረግ የአውሊያዎችን በረካ የሚያስገኙ ተግባራት ናቸውይላሉ፡፡ ሺዓዎችም የኢማሞችን መቃብሮች ማሳመር፤ ደሪህ መገንባት፤ ዚያራ ማድረግ ወዘተበጣም አስፈላጊ ተግባራት እንደሆኑ ያምናሉ፡፡
3.     አህባሾችከኸሊፋ አሊ ኢብን አቡጣሊብ ጋር የተዋጉ ሰሃባዎችን መሳደብና መራገም ሀጢአት የለውምባዮች ናቸው፡፡ ሺኣዎችም በዚህ ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው፡፡
4.     በረመዳን ወር ህዝበ ሙስሊሙ ለተራዊህ ሰላት ወደ መስጊድ ሲሄድ በሀገራችን ውስጥ ያሉት አህባሾ ደግሞኢልም እንማራለንእያሉ ወደ መርከዝ ነው የሚሄዱት፡፡ተራዊህ ለምን አትሰግዱም?” ብሎ ለጠየቃቸው ሰውተራዊህ ሱንና ነው፡፡ ኢልም መማር ግን ፈርድ ነውየሚል መልስ ይሰጣሉ፡፡ ሺዓዎች ደግሞ መስጊድ ሄደው ተራዊህን በጀመዓ አይሰግዱም፡፡ምክንያቱ ምንድነው?” ተብለው ሲጠየቁይህ ዑመር የጀመረው ቢድአ ነውይላሉ፡፡
5.     አህባሾች የሚከተሉት የሱፊ ጠሪቃሪፋዒያይባላል፡፡ ይህ ጠሪቃ ሲልሲላውን (የሼይኾች የቅብብሎሽ መንገድ) ከነቢዩ ጋር የሚያገናኘው የሺዓ አማኞች አስራ ሁለቱ ኢማሞቻችን ናቸው የሚሏቸውን ሰዎች በመቁጠር ነው፡፡
6.     አህባሾች ለመውሊድ ከልክ ያለፈ ፍቅር አላቸው፡፡ ለህጋዊነቱም ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ፡፡ የነቢዩንና (..) የፋጢማ ዛህራን (.) መውሊድ ጨምሮ ሌሎች በርካታ መውሊዶችን ያከብራሉ፡፡ ሺዓዎችም መውሊድን በጣም ይወዳሉ፡፡ እንዲያውም መውሊድ ራሱ የተጀመረው በአህሉ ሱንና ሰዎች ሳይሆን ግብጽን 10ኛው-11ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ባስተዳደሩት የፋጢሚይ ገዥዎች ነው፡፡ ፋጢሚዮች ደግሞ ሺዓዎች እንጂ ሱኒዮች አልነበሩም፡፡
7.     አህባሾች ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህንና ሼይ ሙሀመድ ኢብን አብዱልወሃብን በጣም ይጠላሉ፡፡ ሺዓዎችም በነዚህ ምሁራን ላይ ተመሳሳይ አቋም ነው ያላቸው፡፡
   የአህባሽና የሺዓ መመሳሰል ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል፡፡ ይሁንና አህባሾች እነኝህን አቋሞች የወረሱት ከሺዓዎቹ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ በፊት እንደገለጽኩትአህባሽየሚባለው ፓርቲ ራሱ የተቋቋመው የአንጃው መስራች የሆኑት ሼኽ አብዱላህ አል-ሀረሪ በተበሩክ፤ ተወሱል፤ የመቃብር ዚያራ ወዘተ.. ላይ ለነበራቸው የተዛነፈ አቋም ሸሪአዊ መልክ ለማስገኘት በመፈለጋቸው ነው፡፡
   ሰሀባዎችን መስደብና ተራዊህን ዝቅ አድርጎ ማየት ደግሞ ከሺዓዎች የተወረሰ ሳይሆንአለዊየሚባሉትን የሶሪያ ገዥዎች ለማስደሰት የተወሰዱ አቋሞች ይመስሉኛል፡፡ (ኡለማ ሙሉ በሙሉ ካፊር ነው በማለት የፈረጁት ይህንን አለዊ የሚባለውንፊርቃነው፡፡ ሺዓዎችም ሆኑ ሱኒዮችአለዊ ካፊር እንጂ ሙስሊም ቡድን አይደለምበሚለው ላይ ተስማምተዋል፡፡)
የአህባሽና የሺዓ ልዩነት
አህባሾችና ሺዓዎች በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ከፍተኛ ልዩነት አላቸው፡፡
1.      አህባሾች የሚጠሉት እነ ኢብን ተይሚያህን ብቻ አይደለም፡፡ እነርሱ የሚወዷቸውን የአውሊያ መቃብሮች ያልነኩባቸውን እንደ ጀማሉዲን አል-አፍጋኒ፤ ረሺድ ሪዳ፤ አቡል አእላ መውዱዲ፤ ሰይድ ቁጥብ፤ ወዘተ የመሳሰሉ ምሁራንና ሙስሊም ታጋዮችንም በጣም ይጠላሉ፡፡ ሺዓዎች ግን ለነኝህ የተሀድሶ አራማጆችና የሙስሊም ህብረት አስተማሪዎች ከፍተኛ አድናቆት አላቸው፡፡ ለምሳሌ የቀድሞው የኢራን መሪ አያቱላህ ሩሑላህ ኾሜይኒ የአቡል አእላ መውዱዲን መጽሀፍት ከመውደዳቸው የተነሳ አንዳንዶቹን ወደ ፋርሲ (ኢራን) ቋንቋ ተርጉመዋል፡፡
2.     አህባሾች በዚህ ዘመን የሸሪአ ህግን የሚተገብር መንግስት መመስረት አይቻልም ባይ ናቸው፡፡የኸሊፋዎች አይነት አስተዳደርም ሆነ ኢስላማዊ ሪፐብሊክ መመስረት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ሀይማኖቱን ብቻ ይዘን ከፖለቲካው መገለል አለብንባይ ናቸው፡፡ በአህባሽ አመለካከት መሰረት ጂሀድ እናካሂዳለን የሚሉት የሙስሊም ነጻነት ንቅናቄዎችም ጊዜ አልፎባቸዋል፡፡
   ሺዓዎች ግን ከዚህ ተቃራኒ የሆነ አመለካከት ነው ያላቸው፡፡የሸሪዓ ህግ ከየትኛዉም ዘመን ጋር የሚሄድ ወደር የለሽ ህግ ነው፤ በርሱ የሚመራ ኢስላማዊ መንግስት መመስረትም ይቻላልባይ ናቸው፡፡ጂሀድም ቢሆን ጥቃት ባለበት ጊዜ ሁሉ መካሄድ አለበትይላሉ፡፡
3.     አህባሾች በጣም ጽንፈኛ ናቸው፡፡ ከነርሱ ጋር የማይራመድ፤ የነርሱን ሀሳብ የማይቀበል፤ እነርሱ ሸሪአዊ መልክ ሰጥተው የሚያደርጉትን ድርጊት የሚቃወም ሁሉካፊርነው፡፡
   ሺዓ ግን እንዲህ አይልም፡፡ ማንም ሰው ኢላሀ ኢለላህ ሙሐመዱን ረሱሉላህብሎ ካመነ ሙስሊም ነው፡፡ ከነርሱ የሚለዩትን ሙስሊሞችመንገዱን ለቀዋል፤ ተሳስተዋልነው የሚሉት እንጂካፊርያሉበት ወቅት የለም፡፡
4.     አህባሾች ከሙስሊሞች ይልቅ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችን ይጎዳኛሉ፡፡ የነርሱ ጓደኞች ምዕራባዊያን፤ ጽዮናዊያን፤ የሶሪያው አለዊ (ኑስራኒ) ሀይማኖት ተከታዮች ወዘተ.. ናቸው፡፡ ሺዓዎች ግን እንዲህ አይነት አመል የለባቸውም፡፡ ሚስጢራቸውን እርስ በራሳቸው እንጂ ከአላህ ጠላቶች ጋር አያወሩም፡፡
5.     አህባሾች ዋነኛ ጠላታችንወሃቢያነው ይላሉ፡፡ በነርሱ አመለካከትእስልምናን እያጠፋ ያለውና ወደፊትም የሚያጠፋውወሀቢያ ነው፡፡ በመሆኑም ወሃቢ የሚሉትን ሰው ለአላህ ጠላቶች አሳልፎ ከመስጠት ወደኋላ አይሉም፡፡
   ሺዓዎች ግንዋነኛው የኢስላም ጠላት ጽዮናዊያንና ተባባሪዎቻቸው ናቸውይላሉ፡፡
ከላይ ከቀረበው ንፅፅር እንደምንረዳው መጥፎ የሚባለው ነገር ሁሉ መጥፎነቱ እኩል አይደለም፡፡ ከመጥፎው ሁሉ የተሻለ መጥፎ አለ፡፡ ከመጥፎዎች ሁሉ የሚበልጥ የመጥፎ መጥፎ አለ፡፡
   አህሉሱንና ወል-ጀመዓነኝ የሚለው አህባሽ ከኛ ጋር በብዙ መልኩ የሚለያየውን የሺዓ አንጃ ያህል እንኳ ለኢስላም አይቆረቆርም፡፡ ሺዓዎች የኢስላም ጠላቶችጽዮናዊያን ናቸውነው የሚሉት፡፡ አህባሽየኢስላም ጠላቶች ወሀቢዎች ናቸው ይላል፡፡ አስተግፊሩላህ!!
   የአህባሽ ጠላቶች እኛ ሙስሊሞች ነን፡፡ አላህ ብቻ አይጣላን እንጂ አህባሽና ግብረ አበሮቹ እንደፈቀዳቸው ይበሉን፡፡ እኛ በአላህ ስለምናምን እንደ አህባሽ የኢስላምን ክብር ለአላህ ጠላቶች አናስረክብም፡፡
ድል የኢስላም ነው፡፡ አላሁ አክበር!!!!                          

No comments:

Post a Comment